በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምሥራቅ ጉራጌ ዞን ግጭት የሞቱ የማረቆ ብሔረሰብ ተወላጆች 12 መድረሱ ተገለጸ


በምሥራቅ ጉራጌ ዞን ግጭት የሞቱ የማረቆ ብሔረሰብ ተወላጆች 12 መድረሱ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:11 0:00

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምሥራቅ ጉራጌ ዞን በመስቃን ወረዳ አስተዳደር፣ በመስቃን ቤተ ጉራጌ እና በማረቆ ብሔረሰብ ግጭት፣ ሕይወታቸው ያለፈ የማረቆ ተወላጆች ቁጥር 12 መድረሱን፣ የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ።

በማረቆ ብሔረሰብ በኩል፣ ግጭት በመፍጠር እና በመቀስቀስ የተጠረጠሩ ስድስት ተጠርጣሪዎች እንደተያዙ፣ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ንጉሤ መከ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ካለፈው ሳምንት ወዲህ፣ በአካባቢው አንጻራዊ ሰላም እንደታየ ቢጠቁሙም፣ አሁንም ግን ስጋት መኖሩን፣ የግብርና ምርቶችን መዝረፍን ጨምሮ የውንብድና ወንጅሎች እየተፈጸሙ እንደኾነ፣ አስተዳዳሪው አስረድተዋል።

ከመስቃን ወረዳ አስተዳደር በኩል፣ ምላሽ እና አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ይኹን እንጂ፣ ለደኅንነታቸው ስለሚሰጉ ስማቸውን ያልጠቀሱ የመስቃን ወረዳ ነዋሪ፣ አካባቢውን የመከላከያ ሠራዊት አባላት የሚገኙበት ጥምር የጸጥታ ኀይል እንደተቆጣጠረውና ሁከቱ ቆሞ መረጋጋት እንደሰፈነ ለሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ከመስቃን ቤተ ጉራጌ በኩል፣ በወንጀሉ የተጠረጠሩ ዘጠኝ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን እንደሚያውቁ፣ እኚኹ አስተያየት ሰጪ አክለው ገልጸዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG