በኤምባሲው የመታሰቢያ ዝግጅት ላይ፣ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካዮች፣ ቤተ እስራኤላውያንና ልዩ ልዩ ተጋባዦች ተገኝተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካይ አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን፣ “በተፈጠረው አሠቃቂ አደጋ የተሰማንን ጥልቅ ኀዘን እገልጻለኹ፤” ብለዋል፡፡ እስራኤል እና ኢትዮጵያ፣ መንፈሳዊ ትስስር እንዳላቸው የጠቀሱት አምባሳደሩ፣ “የደረሰው ኀዘን የኹላችንም ነው፤” ሲሉም አክለዋል፡፡
አስተያየታቸውን የሰጡን ቤተ እስራኤላውያንም፣ በሃይማኖታዊ በዓል ወቅት በተፈጸመው ድንገተኛ የሐማስ ጥቃት የደረሰው ሞት እና ጉዳት እጅግ እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ፣ ኀዘናቸውን የገለጹ አካላትን አመስግነዋል፡፡