በዴሞክራቲክ ኮንጎ በጀልባ ላይ ተሳፍረው ከነበሩ ሰዎች 30ዎቹ ሲሰጥሙ 167 ያህሉ የደረሱበት አለመታወቁን የአካባቢው ባለስልጣናት ዛሬ ዕሁድ አስታወቁ።
የምድር ወገብ እና የአካባቢው የጤና ሚኒስቴር ዲድየር ምቡላ 189 የሚሆኑ ሰዎችን ማትረፍ መቻሉን ገልጸው እስካሁን ድረስ ፍለጋችንን ቀጥለናል ብለዋል። ሚኒስትሩ አያይዘው “እስካሁን ድረስ ያገኘነው 30 አስክሬን ብቻ በመሆኑ የሟቾቹ አሃዝ ከዚህ ከፍ ሊል ይችላል” ሲሉ አስታውቀዋል።
ይኸን መሰል አደገኛ የውሃ ላይ አደጋዎች በአካባቢው ከአቅም በላይ በሚጭኑ ጀልባዎች የተነሳ የተለመዱ መሆናቸውም ተገልጿል።
መድረክ / ፎረም