በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢራን እስራኤልን አስጠነቀቀች


የኢራኑ የውጪ ጉድይ ሚኒስትርሁሴን አሚራብዶላሂያን (ፎቶ ኤፒ ጥቅምት Oct. 13, 2023)
የኢራኑ የውጪ ጉድይ ሚኒስትርሁሴን አሚራብዶላሂያን (ፎቶ ኤፒ ጥቅምት Oct. 13, 2023)

የኢራኑ የውጪ ጉድይ ሚኒስትር፤ እስራኤል የጋዛን ጥቃት የማታቆም ከሆነ፣ ከ“ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ” ጋር ባመሳሰሉት ጥቃት ትመታልች ሲሉ ቤሩት ላይ በሰጡት መግለጫ አስጠንቅቀዋል።

ሁሴን አሚራብዶላሂያን በሰጡት ማስጠንቀቂያ፣ እስራኤል ጥቃቷን የማታቆም ከሆነ እና ሄዝቦላ ውጊያውን ከተቀላቀለ፣ ግጭቱ ወደ ቀጠናው ሌሎች ሀገራት ይስፋፋል ብለዋል።

ቤሩት ላይ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የኢራኑ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የሌባኖሱ ሄዝቦላ ሁሉንም የጦርነት ሁኔታዎች እየገመገመ መሆኑን እና እስራኤል በአስቸኳይ በጋዛ ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት እንድታቆም ጠይቀዋል።

እስራኤል ሄዝቦላን ዋና ጠላት አድርጋ የምትመለከት ሲሆን፣ ሄዝቦላ 150ሺሕ ሮኬቶች እና ሚሳኤሎች፣ እንዲሁም በእስራኤል ማንኛውንም ቦታ በትክክል ሊመቱ የሚችሉ ሚሳኤሎች እንዳለው ይገመታል። በ12 ዓመቱ የሶሪያ ጦርነት የተሳተፉ ልምድ ያላቸው በሺሕ የሚቆጠሩ ተዋጊዎች እና ለየት ያለ ወታደራዊ ድሮንም እንዳለው ይነገራል።

የኢራኑ የውጪ ጉዳይ ሚኒስት በቤሩት በስደት የሚገኙትን ከፍተኛ የሐማስ ባለስልጣን ማግኘታቸውም ታውቋል። ///

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG