በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል የአሌፖን አየር ማረፊያ እንደገና ደበደበች


እስራኤል በ እ.አ.አ በመስከረም 1፣ 2022 በአሌፖ የአየር ማረፊያ ላይ ያደረሰችውን ጥቃት የሚያሳይ የሳተላይት ፎቶ (ፎቶ ፋይል Planet Labs PBC)
እስራኤል በ እ.አ.አ በመስከረም 1፣ 2022 በአሌፖ የአየር ማረፊያ ላይ ያደረሰችውን ጥቃት የሚያሳይ የሳተላይት ፎቶ (ፎቶ ፋይል Planet Labs PBC)

እስራኤል በሶሪያ መንግስት እጅ ባለችው አሌፖ የሚገኝን የአየር ማረፊያ ዛሬ መደብደቧ ታውቋል።

በሶሪያ የሰብዓዊ መብት ተቆጣጣሪ ቡድን መሪ የሆኑት ራሚ አብደል ራህማን ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል እንደተናገሩት፣ ካለፈው ሐሙስ ጥቃት ወዲህ እንደገና ሥራ ጀምሮ የነበረው የአየር ማረፊያ፣ በሰዓታት ውስጥ ከአየር ጥቃት እንደደረሰበት አስታውቀዋል።

ባለፈው ሐሙስ በሶሪያ የሚገኙት የደማስቆ እና የአሌፖ አየር ማረፊያዎች በእስራኤል መደብደባቸው ተዘግቧል።

የሶሪያው የመንግስት ቴሌቭዥን ጥቃቱ መፈጸሙን አረጋግጧል።

በጦርነት በተደቆሰችው ሶሪያ፣ መንግስት የደማስቆን እና የአሌፖን አየር ማረፊያዎች ይቆጣጠራል።

ከአሥር ዓመታት በላይ በሶሪያ በሚካሄደው ጦርነት፣ እስራኤል በኢራን የሚደገፉ ኃይሎችን፣ የሌባኖሱን ሄዝቦላ እና የሶሪያን ሠራዊት ከአየር ስታጠቃ ቆይታለች፡፡

///

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG