በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የባዕድ ልሳንን እየቀየጡ የመናገር ልማድን በቋንቋ ፖሊሲው ለማረም እንደሚሠራ ሚኒስቴሩ ገለጸ


የባዕድ ልሳንን እየቀየጡ የመናገር ልማድን በቋንቋ ፖሊሲው ለማረም እንደሚሠራ ሚኒስቴሩ ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:29 0:00

በኢትዮጵያ በንግግር መሀል የውጭ ሀገራትን ልሳናት በጣልቃ እያስገቡ መናገር ፈጽሞ ያልተለመደ አይደለም፡፡ ይኹንና፣ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ፣ በተለይም የእንግሊዝኛ ቃላትን እየቀየጡ መናገር እየገነነ መጥቷል፡፡

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ የቋንቋ መምህሩ አቶ ታመነ ቻላቸው፣ ይህ ዐይነቱ የአነጋገር ልማድ፥ ጉራማይሌ ቋንቋ ተብሎ እንደሚታወቅ ይገልጻሉ፡፡ በዋናነት በብዙኀን መገናኛዎች ላይ የሚቀርቡ ባለሥልጣናት እና ታዋቂ ሰዎች፣ ልማዱን ወደ ማኅበረሰቡ እንዳስተላለፉ ያመለክታሉ፡፡

በልዩ ልዩ ብዙኀን መገናኛዎች ላይ ከ30 ዓመታት በላይ የሠራውና በአኹኑ ወቅት የአሜሪካ ድምፅ ባልደረባ የኾነው ሰሎሞን አባተም፣ ቅይጥ የአነጋገር ልማዱ፥ ብዙኀን መገናኛዎችንም እየፈተነ እንደመጣ የግል ምልከታውን አጋርቶናል፡፡

በባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር የፖሊሲ እና ስትራቴጅ ጥናት እና ምርምር ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አውላቸው ሹመንካ ደግሞ፣ በ2012 ዓ.ም. ወደ ትግበራ የገባው የቋንቋ ፖሊሲ፣ የመንግሥት የሥራ ሓላፊዎችን ጭምር፣ ጉራማይሌ ቋንቋ መጠቀምን እንደሚከለክል፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡ በመጪው 2016 ዓ.ም. ፖሊሲውን ይበልጥ ወደ ማኅበረሰቡ በማዝለቅ ችግሩን ለማቃለል እንደሚጥር፣ ዶክተር አውላቸው ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቀዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG