በዓለም ዙሪያ፣ የሴት ሥራ ፈጣሪዎች እና ነጋዴዎች ቁጥር፣ ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ መጥቷል፡፡ ይኹን እንጂ፣ ሥራ ፈጣሪ ሴቶች የበለጠ ስኬታማነት ለመኾን፥ የብድር ድጋፍን፣ የሞያ እና የንግድ ሥልጠናዎችን ይሻሉ።
በኢትዮጵያ ይህን ክፍተት ለመሙላት፣ ከዐሥር ዓመት በፊት የተቋቋመው የሴቶች ኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ፕሮጀክት፣ ለብዙ ሴት ነጋዴዎች ውጤታማነት ሰፊ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል።
በዓለም ባንክ እና በተለያዩ የውጭ ሀገር መንግሥታት የሚደገፈው ፕሮጀክቱ፣ ከዓለም ባንክ እጅግ ስኬታማ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ ተደርጎ በምሳሌነት እንደሚወሰድ፣ የተቋሙ የኮሙኒኬሽን ሥራ አስኪያጅ ብርሃኔ ሲሳይ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።
ፕሮጀክቱ፣ በስድስት ከፍተኛ የሴት ነጋዴዎች ቁጥር ባላቸው ከተሞች እና በዙሪያቸው በትግበራ ላይ ይገኛል፡፡ ብድር ከወሰዱት ሴቶች ከ90 በመቶ በላይ የሚኾኑቱ፣ በስኬታማነት ብድራቸውን መክፈል የቻሉበት፣ እንዲሁም ከፕሮጀክቱ ጋራ የሚሠሩ የብድር እና የኅብረት ሥራ ተቋማትም በዐቅም የጎለበቱበት እንደኾነ ተቋሙ አስታውቋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም