በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ: የእስራኤል - ሐማስ ጦርነት መቋጫው “የሁለት-ሀገራት መፍትሔ” እንደኾነ ገለጸች


ኢትዮጵያ: የእስራኤል - ሐማስ ጦርነት መቋጫው “የሁለት-ሀገራት መፍትሔ” እንደኾነ ገለጸች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:16 0:00

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም፣ ዛሬ ኀሙስ፣ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት፣ ኢትዮጵያ “የሁለት- ሀገራት የመፍትሔ ሐሳብን” እንደምትደግፍና ይህም የቆየ አቋሟ እንደኾነ ገልጸዋል፡፡

ቃል አቀባዩ፣ ካለፈው ሳምንት ቅዳሜ አንሥቶ እየተባባሰ የቀጠለውን የእስራኤል-ሐማስ ግጭት አስመልክቶ፣ የመንግሥት አቋም ምን እንደኾነ ለተነሣላቸው ጥያቄ ግን፣ መንግሥት ጉዳዩን እየተከታተለ እንደኾነ ከመግለጽ በቀር ሌላ አስተያየት አልሰጡም፡፡

በኢትዮጵያ የፍልስጥኤም ኤምባሲ ትላንት ባወጣው መግለጫ፣ ሐማስን በስም ሳይጠቅስ፣ “የፍልስጥኤም አንጃዎች ራሳቸውን የመከላከል መብታቸውን እንዲተገብሩ ያስገደዷቸው፣ በእስራኤል ሲፈጸሙ የቆዩ በደሎች ናቸው፤” ብሏል፡፡ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም፣ እስራኤል በጋዛ ላይ እያጠናከረች ያለችውን ድብደባ እንዲያወግዝ ጠይቋል፡፡

በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ በበኩሉ፣ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በተጨማሪ፣ የሐማስን ድንገተኛ ጥቃት እንዲያወግዝና ከእስራኤል ጎን እንዲቆም ለኢትዮጵያ መንግሥት ቀጥተኛ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG