በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእስራኤል እና የሐማስ ውጊያ የዓለም አቀፍ ትኩረት ስቧል


የእስራኤል እና የሐማስ ውጊያ የዓለም አቀፍ ትኩረት ስቧል
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:19 0:00

በድንገተኛ የሐማስ ማጥቃት የተጀመረው ውጊያ፣ በእስራኤል እና በጋዛ ላይ ካለው ቀጥተኛ ጉዳት ባለፈ፣ በዓለም ፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ላይ ጉልሕ አሉታዊ ተጽእኖ ሊያስከትል እንደሚችል፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡት የፖለቲካ ተንታኙ ዶር. ሔኖክ ጌታቸው ተናግረዋል፡፡

ተንታኙ፣ ዩናይትድ ስቴትስም በአካባቢው ላይ የምትከተለውን ፖሊሲ እንድታጤን ሊያደርጋት እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

በሌላ በኩል፣ በእስራኤል እና በሐማስ ታጣቂ ቡድን መካከል የሚካሔደው ጦርነት፣ አስቸኳይ እልባት ካልተገኘለት አስከፊ መዘዝ እንደሚኖረው፣ አስተያየታቸውን የጠየቅናቸው ሦስት የዐዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG