በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የምክር ቤት አባላትን በመራጮቻቸው ከወንበራቸው ለማንሣት የተደረገ ውይይት


የምክር ቤት አባላትን በመራጮቻቸው ከወንበራቸው ለማንሣት የተደረገ ውይይት
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:49 0:00

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፥ የምክር ቤት ተቀማጭ እንደራሴዎች፣ የመረጣቸውን ሕዝብ አመኔታ በሚያጡበት ጊዜ ለጥያቄ እንዲጠሩና ከወንበራቸው እንዲነሡ ለማስቻል በአዘጋጀው መመሪያ ረቂቅ ላይ፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋራ ተወያየ፡፡

በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የፖለቲካ ፓርቲዎቹ፣ በመመሪያው ረቂቅ ላይ የሰፈሩትን ድንጋጌዎች ለማስፈጸም፣ የምርጫ ቦርዱ “ብቃቱም ጉልበቱም የለውም፤” ሲሉ ተችተዋል፡፡ ገዥው ፓርቲ የማይፈልጋቸውን የም/ቤት አባላት፣ ከፓርላማው ለማስወገድ መሣሪያ እንዳይኾን፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎቹ ያላቸውን ስጋት አመልክተዋል፡፡

የብሔራዊ ምርጫ ቦርዱ በበኩሉ፣ በሕግ የተሰጠውን ሓላፊነት እና ግዴታ ተግባራዊ ለማድረግ፣ ምንም የሚጎድለው እንደሌለ በመጥቀስ ለትችቱ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG