በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩዋንዳ የተቺዎቿን ድምፅ ለማጥፋት ዓለምአቀፍ ዘመቻ እንደያዘች ሂዩማን ራይትስ ዎች ከሰሰ


የሩዋንዳን መንግሥት፡ የተቃውሞ ድምፅ ወይም ነቀፌታ በሚያቀርቡበት ዜጎች ላይ፣ ድንበር ተሻግሮ፥ የግድያንና ደብዛን የማጥፋት ወንጀሎች ይፈጽማል፤ ሲል፣ ሂዩማን ራይትስ ዎች፣ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ ከሰሰ፡፡

የመብቶች ተሟጋቹ፣ የሩዋንዳን መንግሥት ድርጊት፣ “ድንበር ተሻግሮ” በሚፈጸም የበደል ዐይነት ወንጅሏል።

እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ፣ ገዥው የሩዋንዳ አርበኞች ግንባር፣ ለሥልጣኑ ስጋት አድርጎ በሚያያቸው ላይ ሁሉ ቁጥጥሩን ለማጥበቅ ባለው ፍላጎት፣ “በኃይል እና በአመዛኙም ጉዳት ማድረስ የሚችል ጥቃት ይፈጽማል፤” ብሏል።

ሪፖርቱ አክሎም፣ ከአገራቸው ውጭ በሚኖሩ የመንግሥቱ ተቺ በኾኑ ሩዋንዳውያን ላይ የተፈጸሙ በርካታ የግድያ እና የአፈና ሙከራዎችን፤ እንዲሁም የገቡበት እንዳይታወቅ ማድረግና ሌሎች አካላዊ ጥቃቶችን መመዝገቡን አመልክቷል። በተጨማሪም፣ በነቃፊነት የሚያያቸውን በውጭ አገር የሚኖሩ ዜጎች፣ ተላልፈው እንዲሰጡት የማድረግ ጥረት መኖሩንም፣ ዘገባው አክሎ ጠቁሟል።

የሩዋንዳ መንግሥት ቃል አቀባይ ዮላንዴ ማኮሎ በበኩላቸው፣ ለፈረንሳይ የዜና ወኪል በሰጡት አስተያየት፣ “ሂዩማን ራይትስ ዎች፣ በእርሱ ብቻ ምናብ ያለና የሩዋንዳን ገጽታ የሚያጠለሽ የተዛባ ዘገባ ማቅረቡን ቀጥሏል፤” ብለዋል።

ምሥራቅ አፍሪቃዊቱን አገር፣ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1994፣ በዚያች አገር ከተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ማግስት አንሥቶ የመሩት ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ፣ በሚቀጥለው ዓመት በሚካሔደው ምርጫም፣ የሥልጣን ዘመናቸውን የማራዘም ዕቅድ እንዳላቸው ከወዲሁ ታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG