ከቀድሞ የደቡብ ክልል መንግሥት ሠራተኞች 349ኙ፣ በሲዳማ ክልል ቢመደቡም፣ ክልሉ ግን 223ቱን አልቀበልም ማለቱንና በዚኽም ለእንግልት መዳረጋቸውን፣ ሠራተኞቹ ገለጹ።
"ሲዳምኛ ቋንቋ አትችሉም፤" የሚል ምክንያት በክልሉ እንደተሰጣቸው ለአሜሪካ ድምፅ የገለጹት ሠራተኞቹ፣ በምደባ መስፈርቱ ውስጥ ባልነበረ ቅድመ ኹኔታ በደል ተፈጽሞብናል፤ ሲሉ፣ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
የሲዳማ ክልል የሕዝብ አገልግሎት ቢሮ፣ የክልሉ የሥራ ቋንቋ ሲዳምኛ በመኾኑ፣ ለክልሉ ከተመደቡት መካከል ቋንቋውን የሚችሉትን ብቻ እንደተቀበለ አስታውቋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።