በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዐማራ ክልል የቀጠለው ግጭት ለሰብአዊ ርዳታ ዕንቅፋት እንደኾነበት ኦቻ ገለጸ


 በዐማራ ክልል የቀጠለው ግጭት ለሰብአዊ ርዳታ ዕንቅፋት እንደኾነበት ኦቻ ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:18 0:00

በዐማራ ክልል የቀጠለው ግጭት ለሰብአዊ ርዳታ ዕንቅፋት እንደኾነበት ኦቻ ገለጸ

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ /UN-OCHA/፣ የዐማራ ክልል ወቅታዊ ኹኔታ አለመረጋጋቱን ገለጸ፡፡

ቢሮው ትላንት ባወጣው ዐዲስ መግለጫ፥ በምዕራብ እና ምሥራቅ ጎጃም፣ በሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ በሰሜን ሸዋ እንዲሁም በማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች፣ መረጋጋት እንደማይታይና ግጭቶች እንደቀጠሉ መኾናቸውን ገልጿል፡፡

በክልሉ፣ የሞባይል ዳታ ሙሉ በሙሉ እንደተቋረጠ የጠቀሰው የማስተባበሪያ ቢሮው፣ ይህም ከአለመረጋጋቱ ጋራ ተያይዞ ለሰብአዊ ርዳታ ሥራ ዕንቅፋት እንደኾነ፣ በሪፖርቱ አመልክቷል፡፡

በባሕር ዳር ከተማ የሚኖሩና የጭነት መኪና ባለንብረት የኾኑ አንድ ግለሰብ፣ በክልሉ ባለው ወቅታዊ አለመረጋጋት ምክንያት፣ ከክልሉ ወደ የትኛውም የአገሪቱ ክፍሎች ለመውጣትም ኾነ ለመግባት አስቸጋሪ ጊዜ እንደኾነ ገልጸውልናል፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው አንድ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህርም፣ በክልሉ የኢንተርኔት ትይይዝ በመቋረጡ፣ በመማር ማስተማር ሒደቱ እና በምርምር ሥራ ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደሩን አመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG