ግሪክ፣ ልክ እንደ ጣልያን፣ በሕገ ወጥ ፍልሰተኞች የመጥለቅለቅ ችግር ገጥሟታል። አገሪቱ፣ ፍልሰቱን ለማስቆም ብቻ ሳይኾን፣ ፍልሰተኞቹን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ፣ የአውሮፓ ኅብረት አባል ሀገራት በአንድነት እንዲሠሩ ግፊት በማድረግ ላይ ነች፡፡
በዚኽ ሳምንት፣ በስፔን በሚደረገው የመሪዎች ጉባኤ ላይ፣ ግሪክ ሐሳቡን እንደምታቀርብ ይጠበቃል። በ27 የአውሮፓ ኅብረት አባላት መካከል ስምምነት እንዲኖር ለማድረግ ግን ሊከብድ እንደሚችል ተመልክቷል፡፡
የቪኦኤዋ አንቲ ካራሳቫ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።