በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትግራይ ክልል በሽግግር ፍትሕ ሥርዐቱ ላይ ጥያቄዎች እንዳሉት ጊዜያዊ አስተዳደሩ አስታወቀ


የትግራይ ክልል በሽግግር ፍትሕ ሥርዐቱ ላይ ጥያቄዎች እንዳሉት ጊዜያዊ አስተዳደሩ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:27 0:00

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ በኢትዮጵያ ሊተገበር በታቀደው የሽግግር ፍትሕ ሥርዐት ላይ ጥያቄዎች እንዳሉት አስታወቀ፡፡

የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ሓላፊ አቶ ዐማኑኤል አሰፋ፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ “አሁን ያሉት የአገሪቱ ተቋማት፣ አሠራሩን ለማስፈጸም የገለልተኝነት ችግር አለባቸው፤” ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሚተገበር የሽግግር ፍትሕ ሥርዐት፣ የውጭ ኀይሎች በትግራይ ክልል ፈጽመውታል ያሉትን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት የማየት ሥልጣን እንደማይኖረው፣ ሓላፊው ተናግረዋል፡፡ በውጭ ኀይሎች የተፈጸሙት የመብቶች ጥሰት፣ በዓለም አቀፍ ተቋማት መታየት እንዳለባቸው የገለጹት አቶ ዐማኑኤል፣ የሀገር ውስጥ የሽግግር ፍትሕ ሥርዐት፣ የእነርሱን ሚና ሊተካው እንደማይገባ አመልክተዋል፡፡

የትግራይ ክልል፣ በሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ዝግጅት ላይ መሳተፍ ሲገባው እንዳልተሳተፈ፣ አቶ ዐማኑኤል አክለው አስታውቀዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ ከፍትሕ ሚኒስቴር እና ከሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ዝግጅት የባለሞያዎች ቡድን፣ አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለዛሬ አልተሳካም፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG