በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ፣ የኦሞ ወንዝ ሞልቶ እና አቅጣጫውን ስቶ በመውጣቱ፣ በውኃ ተከብበው ከነበሩት 60ሺሕ ገደማ አርብቶ አደሮች ውስጥ አብዛኛዎቹ ወደ ደረቅ ስፍራዎች እንደወጡና በሦስት የተለያዩ ቦታዎች እንደተጠለሉ፣ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ፍቅረ ማርያም አይመላ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ።
የኦሞ ወንዝ ሙላት በየጊዜው የሚያደርሰው ጉዳት እየከፋ እንደመጣ ያስታወቀው ወረዳው፣ መንግሥት ዘላቂ መፍትሔ እንዲያበጅለት አመልክቷል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።