በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ልጆች ከባህል ግጭት ጫናዎች ተጠብቀው ማንነታቸውን እንዲያከብሩ የሚጥረው የግንዛቤ ማጎልበቻ መርሐ ግብር


ልጆች ከባህል ግጭት ጫናዎች ተጠብቀው ማንነታቸውን እንዲያከብሩ የሚጥረው የግንዛቤ ማጎልበቻ መርሐ ግብር
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:56 0:00

የስደተኛ ቤተሰብ ልጆች፣ አብዛኛውን ጊዜ፣ የሁለት ባህሎች ግጭት እንደሚያጋጥሟቸው ጥናቶች ያሳያሉ። ልጆቹ፣ ወላጆቻቸው በተወለዱበት ሀገር እና አሁን እየኖሩበት ባለው ሀገር ማንነት መካከል እንደማደጋቸው፣ በሚገጥማቸው የባህል ግጭት፥ ለድባቴ እና ጭንቀት ይዳረጋሉ፤ በቀላሉ የማያስታርቁት የማንነት ጥያቄም ይፈትናቸዋል። በውጪው ዓለም በሚያድጉ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያንም፣ መሰል ችግሮች ይታዩባቸዋል፡፡

በቨርጂኒያ ግዛት አሌግዛንድሪያ ከተማ የቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን፣ በክረምቱ ወራት፥ ልጆች ባህላቸውን እንዲያውቁ፣ በባህል ግጭት ምክንያት ለሚከሠቱ ጥያቄዎቻቸው ምላሽ እንዲያገኙና ራሳቸውን ኾነው በአመራር ጥበብ እና ክህሎት እንዲልቁ፣ በልዩ መርሐ ግብር ግንዛቤን ሲያጎለብት ቆይቷል።

መርሐ ግብሩ በዋናነት፣ ከ6 እስከ 25 ዓመት ዕድሜ መካከል ለሚገኙ ሕፃናት እና ወጣቶች ቢዘጋጅም፣ በማንኛውም እምነት እና ባህል ያሉ ሰዎች እንዲሳተፉበት የተመቻቸ እንደኾነ፣ አስተባባሪዎቹ ገልጸዋል። ባህል፣ ማንነት፣ ግብረ ገብ፣ የአመራር ክህሎት፣ በትምህርት ቤት የአቻ ግፊት ዓይነቶች እና እነርሱን

ለመቋቋም የሚያስችሉ ክህሎቶችን ያካተተ፣ የግንዛቤ ማጎልበቻ መርሐ ግብር እንደኾነ ተሳታፊዎቹ ይገልጻሉ።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG