በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ወንጀሎችን ተጠያቂነት ለማረጋገጥ የሕግ እና የተቋማት ማሻሻያ እንዲደረግ ተጠቆመ


በኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ወንጀሎችን ተጠያቂነት ለማረጋገጥ የሕግ እና የተቋማት ማሻሻያ እንዲደረግ ተጠቆመ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:17 0:00

በኢትዮጵያ፣ የዓለም አቀፍ ወንጀሎችን ተጠያቂነት ከማረጋገጥ አንጻር፣ የሕግ እና የተቋማት ክፍተቶች መኖራቸውን፣ አንድ ጥናት ጠቆመ፡፡

የኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ፣ በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸሙትን ጨምሮ አንዳንድ ዓለም አቀፍ ወንጀሎችን ያላካተተ፣ በሌሎቹ ላይ ደግሞ ግልጽነት እንደሚጎድለው፣ “የሕግ ባለሞያዎች ለሰብአዊ መብቶች” የተባለ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ባደረገው ጥናት አስታውቋል፡፡

የተቋማት የገለልተኝነት ጥያቄም በሽግግር ፍትሕ ሒደቱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ሊኖረው እንደሚችል የጠቆሙት የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አምኃ መኰንን፣ አፋጣኝ መፍትሔ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል፡፡

በዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህሩ ዶር. ዮናስ ቢርመታ በበኩላቸው፣ ዓለም አቀፍ ሕግንና ተሞክሮን ታሳቢ ያደረገ የማሻሻያ ርምጃ መወሰድ እንዳለበት፣ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

የሽግግር ፍትሕ ሒደቱን በበላይነት የሚመራው የፍትሕ ሚኒስቴር፣ ገለልተኛ ባለሞያዎችን ያሳተፈና ተኣማኒ ሒደቶችን የተከተለ ሥራ እንደሚያከናውን፣ ቀደም ሲል በተለያዩ መድረኮች መግለጹ ይታወሳል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG