በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ክልሎች የትምህርት ዘመኑን የተማሪዎች ምዝገባ ዕቅዳቸውን እንዳላሳኩ እየገለጹ ነው


ክልሎች የትምህርት ዘመኑን የተማሪዎች ምዝገባ ዕቅዳቸውን እንዳላሳኩ እየገለጹ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:23 0:00

- በዐማራ ክልል ከሦስት ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ወደ ት/ቤት አልተመለሱም

በኢትዮጵያ በልዩ ልዩ አካባቢዎች ባለው ግጭት እና አለመረጋጋት፣ እንዲሁም በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች የተነሳ፣ በያዝነው የትምህርት ዘመን፣ ወደ ትምህርት ቤት የሚገቡ ተማሪዎች ብዛት እንዳሽቆለቆለ እየተገለጸ ይገኛል፡፡

በዚኽ ዓመት፣ 6ነጥብ2 ሚሊዮን ተማሪዎችን ለመመዝገብ ዐቅዶ እንደነበረ የገለጸው የዐማራ ክልል ትምህርት ቢሮ፣ በክልሉ ባለው የትጥቅ ግጭት ምክንያት፣ ከ3ነጥብ2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዳልተመለሱ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቋል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልም፣ 305ሺሕ ተማሪዎችን ለመመዝገብ ቢያቅድም፣ “ዕቅዴን ለማሳካት አልቻልኹም፤” ብሏል፡፡

በዘንድሮ የትምህርት ዘመን፣ በመላ አገሪቱ የተመዘገቡ ተማሪዎችን ቁጥር አስመልክቶ፣ ከትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG