በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፈተናዎች ንብርብር ውስጥ ለሚገኘው የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሻሻሉ ተስፋዎች አሉ?


በፈተናዎች ንብርብር ውስጥ ለሚገኘው የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሻሻሉ ተስፋዎች አሉ?
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:39 0:00

በኢትዮጵያ በአምራች ዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች፣ ምርታማነታቸውን የሚፈታተኑ የተነባበሩ ችግሮች እንዳሉባቸው ይነገራል፡፡ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ የአጎዋ ነጻ የንግድ ስምምነት መታገድ፣ እንዲሁም አገራዊ የጸጥታ እና የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ ከፈተናዎቹ መሀከል የሚጠቀሱ እንደኾኑ፣ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶቹ ይገልጻሉ፡፡

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪያል ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አክሊሉ ታደሰ፣ በ2014 ዓ.ም. በኮቪድ-19 እና በጦርነቱ ምክንያት፣ ሰባት የውጭ ኩባንያዎች ለቀው እንደወጡ ያስረዳሉ፡፡

በአጎዋ መታገድ ምክንያት ግን የወጣ ፋብሪካ እስከ አሁን እንደሌለ፣ ለአሜሪካ ድምፅ የተናገሩት ሓላፊው፣ ከዚኽ ይልቅ፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት፣ 67 ዐዲስ ባለሀብቶች ወደ ፓርኮቹ እንደገቡ አስታውቀዋል፡፡

በዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህር ዶክተር አጥላው ዓለሙ በበኩላቸው፣ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትንም ኾነ አምራች ኢንዱስትሪውን ሊያሳድጉ የሚችሉ አመቺ አገራዊ ኹኔታዎች አልነበሩም፤ ይላሉ፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG