በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዋግ ኽምራ ዞን በረኀብ ምክንያት ሰዎች እንደሞቱ ተነገረ


በዋግ ኽምራ ዞን በረኀብ ምክንያት ሰዎች እንደሞቱ ተነገረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:39 0:00

በዐማራ ክልል በዋግ ኽምራ ዞን ሦስት ወረዳዎች በተከሠተው ድርቅ ሰዎች እየሞቱ እንደኾነ፣ የአካባቢው ባለሥልጣናት ተናገሩ፡፡

በዞኑ፣ ካለፈው ዓመት አንሥቶ በተከሠተው ድርቅ ምክንያት፣ በተለይ በሰሀላ ሰየምት ወረዳ ባለፈው አንድ ወር ብቻ አራት ሰዎች እና በሺሕዎች የሚቆጠሩ የቤት እንስሳት እንደሞቱ፣ ባለሥልጣናቱ ዛሬ ሰኞ ለአሜሪካ ድምፅ አረጋግጠዋል፡፡

አካባቢው ዝናም አጠር በመኾኑ፣ ሕዝቡ የርዳታ እህል እየተሰፈረለት ይኖር እንደነበር፣ የሰሀላ ሰየምት ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ብሩ ተናግረዋል። ለአካባቢው የርዳታ እህል ሲያከፋፍሉ የነበሩ ለጋሽ ድርጅቶች፣ ድጋፍ ማቆማቸውና ዘንድሮም ዝናም አለመዝነሙ ችግሩን እንዳባባሰው፣ አቶ ሲሳይ ብሩ ገልጸዋል፡፡

አስቸኳይ የምግብ ርዳታ ወደ በቅርቡ ወረዳው ካልተላከ፣ ከ42ሺሕ በላይ ሕዝብ ለአደጋ እንደሚጋለጥ፣ የወረዳው ሓላፊው ጠቁመዋል፡፡

የዞኑ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ሓላፊ አቶ ከፍያለው ደባሽ በበኩላቸው፣ በአበርገሌ፣ ጻግብጂ እና ሰሀላ ሰየምት ወረዳዎች፣ ከፍተኛ ድርቅ እንደተከሠተ አረጋግጠው፣ በተለይ በሰሀላ ሰየምት ወረዳ፣ ርዳታ በቅርቡ በአውሮፕላን ካልደረሰ፣ በሳምንታት ጊዜ ውስጥ ብዙ ሰዎች ሊሞቱ እንደሚችሉ፣ ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

የዐማራ ክልል የአደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ቅድመ ማስጠንቀቂያና ምላሽ ኮሚሽን ዲሬክተር አቶ ብርሃኑ ዘውዱ፣ በአካባቢው፣ በመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች እና በፋኖ ታጣቂ ቡድን መካከል የተስፋፋው ግጭት፣ ወደ አካባቢው የርዳታ እህል ለማጏጏዝ ዕንቅፋት እንደኾነ አመልክተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG