በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዙባብዌ በደረሰ የማዕድን አደጋ ሠራተኞች ሞቱ


ፎቶ ፋይል (ሮይተርስ)
ፎቶ ፋይል (ሮይተርስ)

በዚምባብዌ በአንድ ማዕድን ማውጫ በደርሰ አደጋ አራት ሠራተኞች ሲሞቱ፣ አምስት የሚሆኑት አሁንም በናዳው ውስጥ ተቀብረው እንደሚገኙ ታውቋል።

አደጋው ከመዲናዋ ሃራሬ 120 ኪ ሜ ላይ በሚገኝ የማዕድን ማውጫ ትናንት ዓርብ መድረሱ ታውቋል።

21 የሚሆኑ ሠራተኞችን ማዳን መቻሉ ተገልጿል።

የዚምባብዌ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬርሽን በበኩሉ፣ 18 ሰዎች በጉድጓዱ ውስጥ ተቀብረው ሊሆን እንደሚችል ዘግቧል።

ከአራት ዓመት በፊት በደረሰ አደጋ፣ አንድ የማዕድን ማውጫ ጉድጓድ በጎርፍ በመጥለቅለቁ 24 ሠራተኞች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG