በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ አራት የዩክሬን ግዛቶችን ወደራሷ የቀላቀለችበትን አንደኛ ዓመት አከበረች


ቭላድሚር ፑቲን (ፎቶ ኤኤፍፒ መስከረም፣ 29, 2023)
ቭላድሚር ፑቲን (ፎቶ ኤኤፍፒ መስከረም፣ 29, 2023)

ሩሲያ ከዩክሬን አራት ግዛቶችን ነጥቃ የቀላቀለችበትን አንደኛ ዓመት በማስመልከት በቴሌቪዥን ንግግር ያደረጉት ቭላድሚር ፑቲን፣ በዶነትስክ፣ ሉሃንስክ፣ ዛፕሮዤዢያ እና ኬርሶን ክልል ያሉ ነዋሪዎች በቅርቡ ባካሄዱት ምርጫ ከሩሲያ ጋር ለመሆን ያላቸውን ፍላጉት አሳይተዋል ብለዋል።

ባለፈው ዓመት የተደረገውን ሕዝበ ውሳኔም ሆነ በቅርቡ የተደረገውን ምርጫ የምዕራቡ ዓለም ሀሰተኛ ሲል አውግዟል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የዩክሬን ኃይሎች ሩሲያ ከለቀቀቻቸው 40 ድሮኖች ውስጥ 30ውን መትተው መጣላቸውን አስታውቀዋል። ኢራን ሠር ካማካዚ ድሮኖች መሆናቸው ታውቋል። ሮማኒያ በበኩሏ በድብደባው ወቅት የአየር ክልሏን ጥሶ ካለፈቃድ የገባ ድሮን ሳይኖር እንዳልቀረ የአየር ኃይሏ አስታውቋል።

በሌላ በኩል፣ ነገ ከሚጀምረው የፈርንጆቹ ጥቅምት ወር ጀምሮ 130 ሺሕ የሚሆኑ ወንዶችን ለአስገዳጅ ወታደራዊ አገልግሎት መመልመል እንደሚጀምር የሩሳያ መከላከያ ሚኒስትር ትናንት አስታውቋል።

ወደ ሩሲያ በተቀላቀሉት ክልሎችም ምልምላው እንደሚካሄድ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ምልምሎቹ በቀጥታ በጦርነት እንዲሳተፉ የሚደረግ ሳይሆን፣ በተጠባባቂነት የሚያዙ መሆናቸውም ታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG