በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአሜሪካ የመንግሥት ሥራ ከዛሬ እኩለ ሌሊት ጀምሮ ሊዘጋ ይችላል


የም/ቤቱ አፈ ጉባኤ ከቪን ማካርቲ (ፎቶ ኤፒ መስከረም 29፣ 2023)
የም/ቤቱ አፈ ጉባኤ ከቪን ማካርቲ (ፎቶ ኤፒ መስከረም 29፣ 2023)

በአሜሪካ የተወካዮች ም/ቤት የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት ጊዜያዊ በጀት እንዲደጽድቅ ባለመደገፋቸው፣ በሀገሪቱ አቆጣጠር ከዛሬ እኩለ ሌሊት በኋላ የመንግስት ሥራ የመዘጋቱን ዕድል አስፍቶታል።

ለአጭር ግዜ የሚዘልቅ በጀት ማጽደቁ ከሜክሲኮ ጋር ያለው ድንበር ጥበቃ እንዲቀጥል እና የም/ቤቱ ዓባላት በበጀቱ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ለመወያየት ግዜ ለማግኘት እጅግ አስፈላጊ ነበር ሲሉ የም/ቤቱ አፈ ጉባኤ ሪፐብሊካኑ ከቨን ማካርቲ ተናግረዋል። ሃሳቡ ግን በወግ አጥባቂ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላቱ ውድቅ ሆኗል።

ከሴኔቱ የሚመጣው የበጀት ሃሳብም በም/ቤቱ ተቀባይነት እንደማያገኝ፣ ማካርቲ ቀድሞ ትዊተር እሁን X በሚል በሚታወቀው የማሕበራዊ ሚዲያ መድረክ ላይ ገልጸዋል። በጉዳዩ ላይ ትናንት ምሽት ከፓርቲያቸው የም/ቤት አባላት ጋር የተነጋገሩበት መሆኑን እና የማለፍ ዕድል እንደማይኖረው እንደተረዱ ማካርቲ አስታውቀዋል።

ለሚቀጥለው 12 ወራት የሚውል በጀት ለማጽደቅ ም/ቤቱ እና ሴኔቱ ስምምነት ላይ ባለመድረሳቸው፣ ከዛሬ እኩለ ሌሊት ጀምሮ የመንግስት ሥራ የመዘጋቱ የማይቀር መስሉ ታይቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG