በዐማራ ክልል ልዩ ልዩ አካባቢዎች በየጊዜው በሚከሠቱ ግጭቶች፣ የአቅርቦት ችግር እንደገጠማቸው ነጋዴዎች ገለጹ፡፡
በባሕር ዳር ከተማ በግብርና እና በኢንዱስትሪ ምርቶች ንግድ የተሰማሩ ነጋዴዎች፣ ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ በክልሉ የተስፋፋውን የጸጥታ መደፍረስ ተከትሎ መንገድ በመዘጋቱ፣ ከመሀል ሀገርም ኾነ በቅርብ ርቀት ካሉ ከተሞች፣ ግብዓቶችን ማስገባት እንዳልቻሉና የአቅርቦት እጥረት እንደገጠማቸው ተናግረዋል፡፡ ሸማቾችም፣ የችግሩ ተጋሪ እንደኾኑ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡
የዐማራ ክልል የንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ በበኩሉ፣ የምርቶች እና ሸቀጦች መጓጓዝ በሚኖርበት ጊዜ በእጀባ አገልግሎት ችግሩን ለመፍታት፣ ከኮማንድ ፖስቱ ጋራ እየተነጋገረ እንደኾነ አስታውቋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።