በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በመቐለ የጮምዓ መስቀል በዓል ከሦስት ዓመት መታጎል በኋላ በድምቀት ተከበረ


በመቐለ የጮምዓ መስቀል በዓል ከሦስት ዓመት መታጎል በኋላ በድምቀት ተከበረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:32 0:00

የመስቀል ደመራ በዓል፣ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ፣ ትላንት ረቡዕ፣ መስከረም 16 ቀን 2016 ዓ.ም. በጮምዓ ተራራ ላይ በድምቀት ተከብሯል፡፡ ክልሉን መነሻ ባደረገውና ለሁለት ዓመት በዘለቀው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ተጽእኖ ሳቢያ ተስተጓጉሎ የቆየው የበዓሉ አከባበር፣ በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ከተቋጨ በኋላ፣ ዘንድሮ በድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡

ከጦርነት በኋላ ያለ የበዓል አከባበር እንደመኾኑ፣“ለሕዝቡ የሥነ ልቡና ግንባታ ድርሻ አለው፤” ሲሉ፣ ተሳታፊ አገልጋዮች እና ምእመናን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል፣ በዓሉ በክልሉ እየተከበረ ያለው፣ “የትግራይ ሰማዕታትን ለመዘከር ኀዘን ለማወጅ በተዘጋጀንበት ጊዜ ነው፤” ያሉት የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ በቀጣይ ሳምንት፣ በጦርነቱ ሕይወታቸው ያለፉ የቀድሞ ተዋጊዎች መርዶ በይፋ እንደሚነገር አስታውቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG