በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በርዳታ አቅርቦት የቀበሌ መታወቂያ ጥያቄ ላይ ተፈናቃዮች ቅሬታ እያሰሙ ነው


በርዳታ አቅርቦት የቀበሌ መታወቂያ ጥያቄ ላይ ተፈናቃዮች ቅሬታ እያሰሙ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:13 0:00

ከልዩ ልዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በግጭት ምክንያት ተፈናቅለው ከማኅበረሰቡ ጋራ ተቀላቅለው የሚገኙ ተፈናቃዮች፣ በርዳታ አሰጣጥ ላይ ቅሬታ እንዳላቸው ተናገሩ፡፡ ከኦሮሚያ እና ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች ተፈናቅለው በባሕር ዳር ከተማ የሚገኙና የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ተፈናቃዮች፣ “የቀበሌ መታወቂያ ካልያዛችኹ ርዳታ ማግኘት አትችሉም፤” እንደተባሉ ሲገልጹ፤ በደብረ ብርሃንና በደቡብ ወሎ-ሐርቡ ከተሞች የሚኖሩቱ ደግሞ፣ “ርዳታ እየቀረበልን አይደለም፤” ብለዋል፡፡

ከልዩ ልዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በግጭት ምክንያት ተፈናቅለው ከማኅበረሰቡ ጋራ ተቀላቅለው የሚገኙ ተፈናቃዮች፣ በርዳታ አሰጣጥ ላይ ቅሬታ እንዳላቸው ተናገሩ፡፡

ከኦሮሚያ እና ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች ተፈናቅለው በባሕር ዳር ከተማ የሚገኙና የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ተፈናቃዮች፣ “የቀበሌ መታወቂያ ካልያዛችኹ ርዳታ ማግኘት አትችሉም፤” እንደተባሉ ሲገልጹ፤ በደብረ ብርሃንና በደቡብ ወሎ-ሐርቡ ከተሞች የሚኖሩቱ ደግሞ፣ “ርዳታ እየቀረበልን አይደለም፤” ብለዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ የጠየቅነው፣ የዐማራ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን፣ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ከድርሻቸው በላይ በተደጋጋሚ ርዳታ የሚወስዱ ሰዎችን ለመቆጣጠር ያመች ዘንድ የመታወቂያ ጥያቄ ተጀምሮ እንደነበር አውስቷል፡፡ ይኹንና ኮሚሽኑ፣ አንድን ተፈናቃይ በስሙ ከመዘገበ በኋላ ርዳታ ያቀርባል እንጂ የቀበሌ መታወቂያ እንደማይጠይቅ ገልጿል፡፡
የባሕር ዳር ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤትም፣ የቀበሌ መታወቂያ የተጠየቀው ለቁጥጥር ሥራ እንዲያመች ነው፤ ብሏል፡፡

(ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ)

XS
SM
MD
LG