በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፖለቲካዊ ውይይት በአፋጣኝ እንዲጀመር ጠየቀ


የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፖለቲካዊ ውይይት በአፋጣኝ እንዲጀመር ጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:12 0:00

በደቡብ አፍሪካ - ፕሪቶርያ በተደረሰው፣ ግጭትን በዘላቂነት የማቆም የሰላም ስምምነት መሠረት፣ ከፌዴራሉ መንግሥት ጋራ የፖለቲካ ውይይት በአፋጣኝ እንዲጀመር፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጠየቀ፡፡ ጥያቄው፣ ለአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪ ቡድንም እንደቀረበና ምላሽ እየተጠበቀ እንደኾነ፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ሓላፊ አቶ ዐማኑኤል አሰፋ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

ጦርነቱ፣ በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ቢቋጭም፣ መንሥኤ የኾኑት ዋነኛ ችግሮች እንዲፈቱ የሚጠበቀው ግን፣ በፖለቲካዊ ውይይት እንደኾነ ሓላፊው ተናግረዋል፡፡ ሰላሙ ዘላቂነት እንዲኖረውና የክልሉ ሕዝብ በርካታ ችግሮቹን ለመፍታት እንዲችል፣ ፖለቲካዊ ውይይቱ ወሳኝ እንደኾነ፣ አቶ ዐማኑኤል አክለው አመልክተዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ ከሚመለከታቸው የኢትዮጵያ መንግስት ሐላፊዎች አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለዛሬ አልተሳካም፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG