በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮሚያ ክልል ከጸጥታ ችግር ባላነሰ የተጋነኑ ዘገባዎች ቱሪስቶችን እያራቁ እንደኾነ ተጠቆመ


በኦሮሚያ ክልል ከጸጥታ ችግር ባላነሰ የተጋነኑ ዘገባዎች ቱሪስቶችን እያራቁ እንደኾነ ተጠቆመ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:01 0:00

በዐዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል በተጀመረው፣ ሦስተኛው ዙር “የኦሮሚያ ክልል ቱሪዝም ሳምንት” ፣ የክልሉ መንግሥት፣ የኦሮሚያ ቱሪዝም መዳረሻዎችን ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ሀገር ጎብኚዎች በማስተዋወቅ ላይ እንደኾነ ገልጿል፡፡

በክልሉ፣ በቱሪስት አስጎብኚነት ሥራ ላይ የተሰማሩ አካላት፣ በተለይ በክልሉ ምዕራባዊ ክፍል የተባባሱ የጸጥታ ችግሮች እና የመሠረተ ልማት እጥረቶች፣ በአካባቢው በርካታ የቱሪስት መስሕቦች ላይ የተደራሽነት ችግር እንደፈጠሩና አገሪቱንም ጥቅም እያሳጡ እንደሚገኙ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ነጋ ወዳጆ በበኩላቸው፣ የጸጥታ ኹኔታውን አስመልክቶ በብዙኀን መገናኛ የሚተላለፉት ዘገባዎች፣ የተጋነኑና ሚዛናዊ አቀራረብ የጎደላቸው እንደኾኑ ጠቅሰው፣ ከጸጥታ ችግሩ ባላነሰ ጎብኚዎችን በማራቅ ሚና እንዳላቸው ተችተዋል፡፡

ኮሚሽኑ፣ ቱሪዝምን በራሱ እንደ ሰላም ማስፈኛ ዘዴ በመጠቀም እየሠራ እንደኾነ ያስታወቁት አቶ ነጋ፣ መንግሥት የጸጥታ ችግሩን ከመፍታት ባሻገር፣ የክልሉን የቱሪስት መዳረሻዎች እና መሠረተ ልማቶች ለማጎልበት ሰፊ ሙዓለ ነዋይ እያፈሰሰ እንደኾነም አመልክተዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG