በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከኢትዮጵያ ቡና የውጭ ንግድ ገቢ ብዙም ተጠቃሚ እንዳልኾኑ አርሶ አደሮች ተናገሩ


ከኢትዮጵያ ቡና የውጭ ንግድ ገቢ ብዙም ተጠቃሚ እንዳልኾኑ አርሶ አደሮች ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:11 0:00

በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የውጭ ምንዛሬ ግኝት፣ የቡና ሽያጭ ጉልሕ ስፍራ ቢኖረውም፣ ከሚገኘው ከፍተኛ ገቢ ብዙም ተጠቃሚ እንዳልኾኑ፣ አርሶ አደሮች ተናግረዋል፡፡

ይኸውም፣ ምርቱን በቀጥታ ወደ ውጭ መላክ ባለመቻላቸው እንደኾነ ለአሜሪካ ድምፅ የተናገሩት አርሶ አደሮቹ፣ በግብይቱ መሀል ላይ ያሉት ደላሎች የተሻለ ተጠቃሚ እንደኾኑ አመልክተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዲሬክተር አቶ ሻፊ ዑመር፣ አርሶ አደሩ የቡና ምርቱን በራሱ ለውጭ ገብያ በማቅረብ የበለጠ ተጠቃሚ እንዲኾን የሚያስችል አሠራር ለመተግበር ተቋማቸው እየሠራ እንደኾነ አስታውቀዋል፡፡

ባለፈው የ2015 ዓ.ም. ወደ ውጭ ከተላከው 240ሺሕ ቶን ቡና ውስጥ፣ ከ1ነጥብ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ስለመገኘቱ፣ የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG