የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ(ኢዜማ) ፓርቲ ሊቀ መንበር ዶር. ጫኔ ከበደ፣ ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ፣ በጸጥታ አካላት ተይዘው እንደተወሰዱ፣ ፓርቲያቸው አስታወቀ፡፡
የፓርቲው የሕግ እና የአባላት ደኅንነት ጉዳይ መምሪያ ሓላፊ አቶ ሥዩም መንገሻ፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ማብራሪያ፣ ዶር. ጫኔ ከበደን የወሰዷቸው የጸጥታ አካላት፣ ታርጋ በሌለው መኪና የመጡና የፍርድ ቤት የእስር ማዘዣም አለማሳየታቸውን ጠቅሰዋል፡፡
ይህም ሕገ ወጥ አያያዝ እንደኾነ የተቹት ሓላፊው፣ መንግሥት የሕግ የበላይነትን ማክበር እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡
ስለ ጉዳዩ፣ ከኢትዮጵያ የፌዴራል ፖሊስ አስተያየት እና ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት፣ ለዛሬ አልተሳካም፡፡
ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።