በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የማራቶን ሬከርድ ወደ ኢትዮጵያ በመመለሱ እንደተደሰተች አትሌው ትዕግሥት አሰፋ ገለጸች


የማራቶን ሬከርድ ወደ ኢትዮጵያ በመመለሱ እንደተደሰተች አትሌው ትዕግሥት አሰፋ ገለጸች
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:18 0:00

የዓለም ማራቶን ክብረ ወሰንን የሰበረችው ኢትዮጵያዊቷ ትዕግሥት አሰፋ፣ ለክብረ ወሰን ብትሮጥም ያሸነፈችበት ሰዓት ያልጠበቀችው እንደኾነች ተናግራለች።

አትሌት ትዕግሥት፣ ኬንያዊቷ ብሪጂድ ኮስጌ በ2019 የቺካጎ ማራቶን በ2፡14፡04 ይዛው የነበረውን የሴቶች የዓለም ክብረ ወሰን፣ በ2ደቂቃከ11 ሰከንድ በማሻሻል፣ በጀርመን በርሊን የተካሔደውን ዓመታዊ የማራቶን ውድድር፣ የርቀቱን ክብረ ወሰን ሰብራ አሸንፋለች;

አትሌቷ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጠችው አስተያየት፣ “ሬከርዱ ወደ ኢትዮጵያ በመመለሱ በጣም ደስ ብሎኛል። የአገሬን ሕዝብ ደስታ በማየቴም እጅግ በጣም ደስተኛ ነኝ። ሬከርድ እንደምሰብር ባውቅም በዚኽ ልክ ይኾናል ብዬ አልጠበቅኹም ነበር፤” ብላለች።

አትሌቷ፣ በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ ያለውን ቢኤምደብሊው የበርሊን ማራቶን ስታሽንፍ፣ የትላንቱ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ ነው፡፡

የ800 ሜትር ተወዳዳሪ የነበረችው ትዕግሥት፣ ፊቷን ወደ ማራቶን ያዞረችው፣ ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር ላይ፣ በሪያድ በተካሔደ የማራቶን ውድድር ነው፡፡

በሌላ በኩል፣ በወንዶች ምድብ፣ ኬንያዊው ኤሊዩድኪፕቾጌ 2፡02፡42 በኾነ ሰዓት አሸንፏል። ኬንያዊው ቪንሴንት ኪፕኬሞይ እና ኢትዮጵያዊው ታደሰ ታከለ፣ ተከታትለው ሁለተኛ እና ሦስተኛ ወጥተዋል።

የትዕግሥት አሰፋ እና የአትሌት ታደሰ ታከለ አሠልጣኝ ገደመዶ ደደፎአ፣ ለውጤቱ በጣም ብዙ እንደለፋ ገልጾ፣ በሴቶች ማራቶን ውጤት በመምጣቱ ደስታውን ገልጿል። ኤቢሳ ነገሠ፣ ከውድድሩ በኋላ ሁለቱንም በበርሊን አነጋግሯቸዋል።

ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG