ትላንት ቅዳሜ ዕለት በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ መካከል የውጥረት አጀንዳ በሆነው በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የሚደረገው ሁለተኛው ዙር ውይይት ቀጥሏል።
ኢትዮጵያ በዚህ ወር መግቢያ ላይ አራተኛው እና የመጨረሻው ዙር የግድብ ውሃ መሙላቷን አስታውቃ ነበር። ይኸም ድርጊቱ ህገወጥ ነው የሚል ፈጣን የሆነ ውግዘትን ከካይሮ አስከትሏል።
ግብጽ እና ሱዳን በ4.2 ቢሊየን ዶላር ወጭ እየተገነባ ያለው ግድብ የአባይ ውሃን መጠንን ያስንስብናል በማለት አኢትዮጵያ ስምምነት ላይ ከመደረሱ በፊት የውሃ ሙሌቶችን እንዳታደርግ በተደጋጋሚ መጠየቃቸው የሚታወስ ነው።
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቀድሞ ትዊተር በመሰኘት በሚታወቀው በአሁኑ አኤክስ የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን አውታር በኩል ሦስቱ ሀገራት ሁለተኛ ዙር ውይይት በአዲስ አበባ መጀመራቸውን አስታውቋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ “ኢትዮጵያ ውጤታማ የሆነ ድርድር በማድረግ በሶስትዮሽ ውይይቷ አማካኝነት መፍትሄ ለማግኘት ቁርጠኛ ነች” በማለት በኤክስ የማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን አውታር ላይ አስታውቋል።
ግድቡ ሲፈጸም የሚያመርተው የኤሌክትሪክ ሀይል መጠን ሀገሪቱ አሁን ከምታመርተውን በእጥፍ የሚልቅ ሲሆን ይኸም 120 ሚሊየን ህዝብ ላላት ሀገር ትልቅ ማዕከላዊ የልማት እቅድ ነው።
በእርስ በርስ ጦርነት እየታመሰች የምትገኘው ሱዳን ባለፉት ዓመታት በግድቡ ዙሪያ ያላት አቋም ተቀያያሪ ሆኗል። በአንጻሩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በጎርጎሮሳዊያኑ 2025 ቀጠናው እያሰጋ ባለው ድርቅ እና የአየር ንበረት ለውጥ ሳቢያ ግብጽ ሙሉ ለሙሉ ሱዳን ደግሞ በከፊል የውሃ እጥረት ያጋጥማቸዋል ሲል ተንብዩዋል።
መድረክ / ፎረም