በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለአቀረቡት ቅሬታ ምላሽ ያላገኙ ሠራተኞች “ጎዳና ላይ መውጣታችን ነው” ሲሉ አማረሩ


ለአቀረቡት ቅሬታ ምላሽ ያላገኙ ሠራተኞች “ጎዳና ላይ መውጣታችን ነው” ሲሉ አማረሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:53 0:00

የቀድሞ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል መንግሥት ሠራተኞች፣ ወደተለያዩ አራት ዐዲስ ክልሎች የተመደቡበት አሠራር፣ በምርጫቸው ላይ የተመሠረተ ባለመኾኑ ያቀረቡት ቅሬታ ምላሽ ሳያገኝ አምስተኛ ሳምንት እንደተቆጠረ ተናገሩ።

በሺሕዎች የሚቆጠሩት ሠራተኞቹ፣ ወደየምድብ ክልሎቻቸው ለመጓዝ ዝግጅት እንደሌላቸው ገልጸው፣ “ሌላ አማራጭ ስለሌለን ጎዳና ላይ መውጣታችን ነው፤” ሲሉ ምሬታቸውን ገልጸዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ የአሜሪካ ድምፅ የጠየቃቸው፣ የክልሎች ማደራጃ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ሓላፊ አቶ ኑሪዬ ሱሌ፣ የሠራተኞቹን ድልድል ያካሔደው፣ በፌዴራል መንግሥት ተወካይ የሚመራና ጽሕፈት ቤታቸውን ጨምሮ አራቱም ክልሎች በአባልነት የሚገኙበት የጋራ ኮሚቴ እንደኾነ ገልጸዋል፡፡

የሠራተኞቹ አቤቱታ፣ በቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በመታየት ላይ እንዳለ ያስታወቁት ሓላፊው፣ ምላሹም የዘገየው፣ ጉዳዩ ውስብስብ በመኾኑና በሌሎች የራሱ ምክንያቶች ነው፤ ብለዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG