በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋምቤላ ክልል ከ30 በላይ ስደተኞች በረኀብ እና በደረሰባቸው ጥቃት እንደሞቱ ተገለጸ


በጋምቤላ ክልል ከ30 በላይ ስደተኞች በረኀብ እና በደረሰባቸው ጥቃት እንደሞቱ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:44 0:00

“በሌሎችም የአገሪቱ አካባቢዎች ለከፋ ረኀብ ተጋልጠዋል” - ኢሰመኮ

በጋምቤላ ክልል፣ ከረኀብ የተነሳና ምግብ ፍለጋ ከካምፕ ወጥተው ጥቃት የተፈጸመባቸው በድምሩ ቢያንስ 30 ስደተኞች፣ ለኅልፈተ ሕይወት እንደተዳደረጉ፣ ኢሰመኮ አስታወቀ፡፡

በክልሉ፣ 400ሺሕ የሚደርሱ ስደተኞች የሚገኙ ሲኾን፣ እነርሱን ጨምሮ በልዩ ልዩ የአገሪቱ አካባቢዎች፣ ለከፋ ረኀብ እና ለተመጣጠነ ምግብ ዕጦት እንደተጋለጡ፣ ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

የርዳታ ዕጦቱ ምክንያት፣ ዓለም አቀፍ ለጋሾች አቅርቦታቸውን ማቋረጣቸው እንደኾነ የገለጹት የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ፣ አስቸኳይ መፍትሔ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል፡፡

በዐማራ ክልል ዳግም የተቀሰቀሰውና በአጎራባች ሀገራትም ያለው ግጭት፣ የተረጂዎቹ ቁጥር እንዲያሻቀብ እያደረገው እንዳለ፣ ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ አንሥተዋል፡፡

የስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎት የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ በአካል ንጉሴ፣ የምግብ አቅርቦቱ መቆሙ፣ ስደተኞችን ለረኀብ ከማጋለጥ አልፎ የጸጥታ ስጋትም እንደፈጠረ ገልጸዋል፡፡

የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) እና የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተቋም(USAID)፣ “የርዳታ አቅርቦቶች እየተሰረቁ ነው፤” በሚል፣ ከሰኔ ወር ጀምሮ ለኢትዮጵያ የሚያደርጉትን የምግብ ድጋፍ ማቋረጣቸው ይታወሳል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG