በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአገው ለፍትሕ እና ዴሞክራሲ ፓርቲ ሁለት አመራሮቹ በመተከል እንደታሰሩ ገለጸ


የአገው ለፍትሕ እና ዴሞክራሲ ፓርቲ ሁለት አመራሮቹ በመተከል እንደታሰሩ ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:11 0:00

የአገው ለፍትሕ እና ዴሞክራሲ ፓርቲ፣ ሁለት ከፍተኛ የአመራር አባላቱ፣ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ታስረው እንደሚገኙ አስታወቀ፡፡

ባጠቃላይ ታስረው የነበሩት አምስት አመራሮች መሆናቸውን የገለጹት የፓርቲው ሰብሳቢ ዶር. ዐዲሱ መኰንን፣ ከአምስቱ አመራሮች ሁለቱ፣ ካለፈው ዓመት ጳጉሜን 4 ቀን ጀምሮ በእስር ላይ እንደሚገኙና ፍርድ ቤትም እንዳልቀረቡ ገልጸዋል፡፡ ሌሎቹ ሦስት አመራሮች ደግሞ፣ ሁለቱን ለመጠየቅ በሔዱበት ከመስከረም 2 ቀን ጀምሮ ታስረው፣ ዛሬ ረፋድ ላይ ስለመለቀቃቸው ተናግረዋል።

የመተከል ዞን አስተዳዳሪ አቶ ለሜሳ ዋቅወያ በበኩላቸው፣ “ግለሰቦቹ የታሰሩት፣ ከአገው እና ከጉምዝ ሰዎችን መልምለው በጫካ ሲያሠለጥኑ ተገኝተው ነው፤” ብለዋል። የፓርቲ ሊቀ መንበር፣ ውንጀላው ሐሰት ነው፤ ሲሉ አስተባብለዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG