በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጎርፍ በጋምቤላ በርካታዎችን ሲያፈናቅል በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎችም እንደሚያሰጋ ተገለጸ


ጎርፍ በጋምቤላ በርካታዎችን ሲያፈናቅል በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎችም እንደሚያሰጋ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:08 0:00

በጋምቤላ ክልል የባሮ ወንዝ ሞልቶ ባስከተለው ጎርፍ፣ በጋምቤላ ከተማ እና በዘጠኝ ወረዳዎች በርካታ ሰዎችን እንዳፈናቀለ፣ የክልሉ መንግሥት አስታወቀ።

የጋምቤላ ከተማ ጤና ጽሕፈት ቤት ሓላፊ እና የከንቲባው ተወካይ አቶ ሳይመን ቲያቺ፣ ባለፉት አራት ቀናት ውስጥ ስድስት ሺሕ የሚደርሱ ሰዎች ተፈናቅለው በትምህርት ቤቶች እና በደረቃማ አካባቢ ላይ እንደሚገኙ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።

በተመሳሳይ፣ በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች፣ የክረምቱ ዝናም የሚያስከትለው ጎርፍ፣ ከ270ሺሕ በላይ ሰዎች ላይ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ(UN-OCHA) ባለፈው ሳምንት ውስጥ አመልክቷል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG