በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በግዳ አያና ጥቃት አምስት ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ


በግዳ አያና ጥቃት አምስት ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:13 0:00

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ፣ ባለፈው ሳምንት ዐርብ፣ በታጣቂዎች ተፈጸመ በተባለ ጥቃት፣ አምስት ሰዎች እንደተገደሉና የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ተጎጂዎችም እንዳሉ፣ የወረዳው ባለሥልጣናት ተናገሩ፡፡

ከተጎጂዎች አንዱ እንደኾኑና በታጣቂዎቹ በተተኮሰ ጥይት እጃቸውን እንደተመቱ ለአሜሪካ ድምፅ የገለጹ የወረዳው ነዋሪ፣ ጥቃቱ፣ ከነቀምት በአንገር ጉቴ በኩል ወደ ጊዳ አያና ከተማ እያመሩ በነበሩ መንገደኞች ላይ፣ ልዩ ስሙ ድችኦ በሚባል ቦታ እንደተፈጸመና አምስት ሰዎች እንደተገደሉ አስረድተዋል።

የግዳ አያና ወረዳ ሆስፒታልም፣ በጥቃቱ የተጎዱ የአምስት ሰዎች አስከሬንና ሌሎች አምስት ተጎጂዎች፣ከአካባቢው ወደ ሆስፒታሉ እንደመጡ አስታውቋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG