በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አልሸባብ የኢትዮጵያን ወታደራዊ ኮንቮይ አጠቃ


በሶማልያ የአልሸባብ ታጣቂዎች
በሶማልያ የአልሸባብ ታጣቂዎች

የአልሽባብ ታጣቂዎች ዛሬ እሁድ ጧት በሶማሊያ ደቡብ ምዕራብ ግዛት ባኮል በአጀብ ይሄዱ በነበሩ የጭነት ተሽከርካሪዎች (ኮንቮይ) ላይ የደፈጣ ጥቃት ማድረሳቸውን የሶማልያ ባልስልጣናት አስታወቁ፡፡

የደፈጣው ጥቃት ያነጣጠረው በሁለት የተሽከርካሪ ቡድኖች (ኮንቮዮች) ላይ ሲሆን አንደኛው ከሶማልያ የይድ ከተማ ወደ ዋጂድ፣ ሁለተኛው ደግሞ ከኤል ባርዶ ወደ ሁደር ከተማ ሲጓዝ እንደነበር ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ወታደሮች በዋጂድ እና ሁደር የጦር ሠፈር ያላቸው መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ማንነታቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የሶማሌ ክልል ባለሥልጣን ለኢቮኤ እንደተናገሩት ጥቃቱ በጦር ሠፈሮቹ ለሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች የተላኩ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን በሚያጅቡ ወታደሮች ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሁዱር ከንቲባ ኦማር አቡልዳሂ መሀመድ ለቪኦኤ የሶማልኛው ክፍል እንደተናገሩት ወታደሮቹ ደፈጣውን አክሽፈዋል፡፡

በተደረገው የተውኩስ ልውውጥ አማጺዎቹ 50 የሚደርሱ ተዋጊዎችን ያጡ መሆኑን ባለሥልጣኑ አስታውቀዋል፡፡

አልሸባብ ለጥቃቱ ኃላፊነቱ የወሰደ ሲሆን በጥቃቱ 167 ኢትዮጵያውያን ወታደሮችን መግደሉን ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ማወደሙን በርካታ የጦር መሳሪዎችን መማረኩን አስታውቋል፡፡

በሁለቱ ወገኖች የተገለጸው አሃዝ በትክክለኛ ወገን አለመረጋገጡ ተመልክቷል፡፡

በሶማልያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር መሀመድ ለቮኢኤ ሲናገሩ አልሸባብ በማህበራዊ ሚዲያ የተናገረውን “ፕሮፖጋንዳ ” ሲሉ ገልጸውታል፡፡

“ለማጥቃት (የኢትዮጵያን ኃይሎች) ይሞክሩ ይሆናል ይሁን እንጂ ግን ለአስር ደቂቃ እንኳ የኢትዮጵያን መከላከያ ኃይሎች ሊገጥሙ አይችሉም” ብለዋል አምባሳደሩ፡፡

አያይዘውም “ይህ በሚገባ የታጠቀ ፕሮፌሽናል ጦር ነው” አልሸባብን በተመለከተ ሁልጊዜም በሚገባ ይቀጣዋል፣ ስለዚህ ይሄ ጸረ ኢትዮጵያ እና ከጸረ ኢትዮጵያ መከላከያ ፕሮፓጋንዳነት የዘለለ አይደለም፡፡” በማለት የተባለውን አጣጥለዋል፡፡

የደህንነት ምንጮች ለቪኦኤ እንደተናገሩት ደፈጣው እውነት መሆኑን አመልክተው በአልሸባብ የተነገረው እጅግ የተጋነነ ነው ብለዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG