በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለረጅሙ የዩክሬን ጦርነት ራሳችንን እናዘጋጅ - የኔቶ ዋና ጸሀፊ


የኔቶ ዋና ጸሀፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ
የኔቶ ዋና ጸሀፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ

“በዩክሬን ለረጅም ጊዜ ለሚቆየው ጦርነት ራሳችንን ማዘጋጀት አለብን” ሲሉ የኔቶ ዋና ጸሀፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ ዛሬ እሁድ ተናገሩ፡፡

ዋና ጸሀፊው በጀርመን ፈንኬ ለተባለው ቡድን የህትመት ሚዲያ በሰጡት ቃለምልልስ “አብዛኞቹ ጦርነቶች መጀመሪያ ከተጠበቀው ጊዜ በላይ ለረጅም ጊዜ ይቆያሉ” ብለዋል፡፡

“ሁላችንም ሰላም በቶሎ እንዲሰፍን እንፈለጋለን” ያሉት ስቶልተንበርግ “ይሁን እንጂ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ዜለንስኪ እና ዩክሬናውያን መዋጋት ካቆሙ አገራቸው እስከመቸውም እንደማትኖር ማወቅ አለብን” ብለዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሩሲያ የዩክሬን ኦዴሳ ግዛትን ዛሬ እሁድ ማለዳ በድሮን እና ሚሳዬል በተቀናጀ ጥቃት የእርሻ ተቋም ማጥቃቷን የዩክሬን አየር ኃይል በማህበራዊ የመገናኛ ብዙሃን መድረክ ቴሌግራም ላይ ተናግሯል፡፡

በጥቃቱ የደረሰ ጉዳት እስካሁን አልተገለጸም፡፡

በሌላም በኩል ዩክሬን ዛሬማለዳው ላይ ክራይሚያ እና ሞስኮ ላይ የድሮን ጥቃት አካሂዳለች፡፡

የክሪሚያ ባለሥልጣናት የድሮን ጥቃቱ አንድ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ታንኳ በመምታት የእሳት ቃጠሎ ማድረሱ ተናግረዋል፡፡

ወደ ሞስኮ የተላኩ ድሮኖች የከተማዪቱን የአየር ትራፊክ መቆጣጠሪያ ሥርዓት ማወካቸው ተነግሯል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG