በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኤል ቻፖ ልጅ ለአሜሪካ ተላልፎ ተሰጠ


ኦቪዲዮ ጉዝማን (ፎቶ Captura de pantalla መስከረም 15፣ 2023)
ኦቪዲዮ ጉዝማን (ፎቶ Captura de pantalla መስከረም 15፣ 2023)

በእስር ላይ የሚገኘው የአደንዛዥ እጽ አስተላላፊዎች አለቃ ዋኪን ጉዝማን ወይም በስፋት በሚታወቅበት “ኤል ቻፖ” ልጅ የሆነው ኦቪዲዮ ጉዝማን ትናንት ዓርብ ለአሜሪካ ተላልፎ ተሰጥቷል።

በአሜሪካ በሱስ አሳዥነቱና ገዳይነቱ እንዲሁም በሚያስከትለው ማሕበራዊ ቀውስ ተጠቃሽ የሆነው የፌንቲኔል መድሃኒትን በማዘዋወር ክስ እንደሚመሠረትበት ታውቋል።

የፕሬዝደንት ባይደን አስተዳደር የገዳዩን መድሃኒት ሥርጭት ለመግታት በሚያደርገው ጥረት አበረታች እርምጃ ነው ተብሏል።

የአሜሪካው ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ሜሪክ ጋርላን እንዳሉት የኦቪዲዮ ጉዝማን መያዝ ከጉዝማን ቤተሰብ ጋር ግንኙነት ያለው የሲናሎዋ የአደንዛዥ እጽ አዘዋዋሪ ቡድን ላይ አሜሪካ በማድረግ ላይ ያለቸው ዘመቻ አካል ነው።

ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ሜክሲኮ የ 33 ዓመቱ ኦቪዲዮ ጉዝማንን አሳልፋ በመስጠቷ አመስግነዋል።

ኦቪዲዮ ጉዝማን ከአራት ዓመታት በፊት ሜክሲኮ ውስጥ ተይዞ የነበረ ሲሆን፣ ቡድኑ የበቀል ጥቃት በመክፈቱ በፕሬዝደንት አንድሬስ ማኑኤል ሎፔዝ ኦብራዶር ትዕዛዝ እንዲልቀቀ ተወስኗል።

በአሜሪካ በቀን 200 ሰዎችን በመግደል ላይ ያለውን ፌንትኔል የተሰኘ መድሃኒት በሕገ ወጥ መንገድ አምርቶ በማሰራጨት የጉዝማን ቤተሰብ ዋና ተዋናይ ነው ሲሉ የአሜሪካ ባለስልጣናት ይከሳሉ።

ከፍተኛ ሱስ አሲያዥ የሆነው ፌንትኔል በአሜሪካ የምግብና መድሃኒት አስተዳደር ለውጋት ማስታገሻነት የተፈቀደ ቢሆንም፣ በሕገ ወጥ መንገድ እየተመረተ የበርካቶችን ሕይወት እየቀጠፈና ከፍተኛ የማኅበራዊ ቀውስ እያስከተለ ይገኛል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG