የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በሩሲያ የኑክሌር ተሸካሚ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖችን እና ሌሎችንም የጦር አውሮፕላኖችን ተመልክተዋል።
አርቶዮም በተሰኘችው የሩሲያ ምሥራቃዊ ከተማ የሚገኙት ኪም ጆንግ ኡን፣ በሩሲያው የመከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሾዪጉ እና ሌሎች ወታደራዊ አዛዦች ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
ለጉብኝት የቀረቡት መሣሪያዎች ሩሲያ በዩክሬን ወረራ የተጠቀመችበት እንደሆኑ ተጠቁሟል።
ኪም በሩሲያ ያደረጉት ጉብኝት ከሀገሪቱ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር የተደረገን የአራት ሰዓታት ውይይትን እንደጨመረ ታውቋል።
ኪም ወደ ሩሲያ ባደረጉት ጉዞ፣ ሁለቱ መሪዎች ምን ዓይነት ወታደራዊ ስምምነት ሊያደርጉ ይችላሉ የሚለው ጉዳይ የምዕራቡን ዓለም አሳስቦታል።
መድረክ / ፎረም