በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አል ቡርሃን ዩጋንዳ ይገኛሉ


አብደል ፋታህ አል ቡርሃን (ፎቶ ፋይል ኤፒ)
አብደል ፋታህ አል ቡርሃን (ፎቶ ፋይል ኤፒ)

በሱዳን መዲና ካርቱም ጦርነቱ እየተፋፋመ ባለበት ዛሬ ቅዳሜ፣ የሀገሪቱ ጦር ጠቅላይ አዛዥ ጀኔራል አብደል ፋታህ አል ቡርሃን ወደ ዩጋንዳ አቅንተዋል።

ጀኔራሉ እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ ማዘዣ ጣቢያቸው በነበረ ካርቱም በሚገንኝ አንድ ወታደራዊ ዋና መምሪያ፣ በተቀናቃኛቸው ሞሃመድ አምዳን ዳግሎ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በከባድ መሣሪያ ሲደበደብ እንደነበር ነዋሪዎች መናገራቸውን የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

የሱዳን ሉአላዊ ም/ቤት ባወጣው መግለጫ አል ቡርሃን ከዩጋንዳው ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ጋር “በሁለትዮሽ እና ሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ” ይነጋገራሉ ብሏል።

አል ቡርሃን በዩጋንዳ የሚያደርጉት ጉብኝት በቅርብ ሳምንታት ውስጥ የተደረገ ስድስተኛው የውጪ ጉዞ መሆኑ ነው።

ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ብቻ ቡርሃን ወደ ግብጽ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኳታር፣ እና ኤርትራ ተጉዘው ከሀገራቱ መሪዎች ጋር ተነጋግረዋል። ድርድር የሚደረግ ከሆነ ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ ለማሰባሰብ የሚያደርጉት ጥረት እንደሆነ ተንታኞች በመናገር ላይ ናቸው።

ባለፈው ሚያዚያ የጀመረውና እስከ አሁን የ7ሺህ 500 ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል የተባለው ግጭት አሁንም ጋብ አላለም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG