በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የማኅበረሰብ ግብረ ገብነት በኢትዮጵያ - የባለሞያዎች አስተያየት


የማኅበረሰብ ግብረ ገብነት በኢትዮጵያ - የባለሞያዎች አስተያየት
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:58 0:00

ኢትዮጵያ፣ ከንጉሣዊ ሥርዐቱ መውደቅ በኋላ የተከተለቻቸው የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ርእዮቶች፣ ለአገሪቱ የማኅበረሰባዊ ግብረ ገብነት ዕሤት መሸርሸር አስተዋፅኦ ማድረጋቸውን፣ በዘርፉ ላይ የሚሠሩ ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡

ከሌሎች ልዩ ልዩ ተጠቃሽ ምክንያቶች ጋራ፣ ማኅበራዊ ብዙኀን መገናኛዎች፣ በአገሪቱ የግብረ ገብነት ዕሤት፣ እንደ ማኅበረሰብ በየጊዜው እየሣሣ እንደመጣ አመላካች መድረኮች እንደኾኑ፣ ባለሞያዎቹ ያስገነዝባሉ፡፡

ግብረ ገባዊ ዕሤቱ ወደነበረበት የማኅበራዊ አስተሳሰብ ደረጃ እንዲመለስ፣ መሠረቱ የኾነው ቤተሰብ በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ፣ ባለሞያዎቹ ያሳስባሉ፡፡ በዚኽ ረገድ፣ በግብረ ገብ የታነፁ ተስፋ ሰጪ ወጣቶች ሲወጡ እየታዩ እንደኾነም ያመለክታሉ፡፡

አስማማው አየነው፣ በማኅበረሰብ ግብረ ገብነት አስተሳሰብ እና ዕሤት ላይ፣ መጻሕፍት ያዘጋጁትን ዶክተር ኤርሲዶ ለንደቦንና በሕይወት ክህሎት ሥልጠና ላይ የሚሠሩትን አቶ ብርሃኑ ራቦን አናግሮ ያሰናዳውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG