በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፍሪካ በግጭት በተዘጉ ትምህርት ቤቶች ሳቢያ የሚሊዮኖች ሕፃናት ትምህርት ለአደጋ ተጋልጧል


በአፍሪካ በግጭት በተዘጉ ትምህርት ቤቶች ሳቢያ የሚሊዮኖች ሕፃናት ትምህርት ለአደጋ ተጋልጧል
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:11 0:00

በስምንት የአፍሪካ ሀገራት፣ በጸጥታ መደፍረስ፣ ከ13ሺሕ200 በላይ ትምህርት ቤቶች እንደተዘጉና በዚኽም ምክንያት፣ ቢያንስ 2ነጥብ5 ሚሊዮን ሕፃናት ከትምህርት ገበታ ውጪ እንደኾኑ፣ ሦስት ዓለም አቀፍ ተቋማት በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታወቁ፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ ባለፈው ሳምንት የጋራ መግለጫ ያወጡት፥ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት(UNHCR)፣ የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት(UNCIEF) እና የኖርዌይ የስደተኞች ምክር ቤት፣ በአህጉሩ፣ ግጭትን ተከትሎ በሚዘጉ ትምህርት ቤቶች፣ የሚሊዮኖች ሕፃናት ትምህርት ለአደጋ እንደተጋለጠ አመልክተዋል፡፡

ተቋማቱ፣ ባለፉት አራት ዓመታት ባጋጠሙ የትምህርት ቤቶች መዘጋት ላይ ባወጡት መረጃ መሠረት፣ በሳህል ቀጣና ውስጥ ብቻ የተዘጉት ትምህርት ቤቶች ቁጥር በአምስት እጥፍ ጨምሮ ከ1ሺሕ700 ወደ 9ሺሕ አድጓል። ከነዚኽ ትምህርት ቤቶች ደግሞ ሁለት ሦስተኛው የሚገኙት በቡርኪናፋሶ ነው።

በዚኽ ዙሪያ መሐመድ ዩሱፍ ከናይሮቢ ያደረሰንን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG