በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጋልሙዱግ ፕሬዚዳንት ከግድያ አመለጡ


በማዕከላዊ ሶማልያ መዱግ ክልል፣ ዱሳማረብ ከተማ እአአ ታኅሳሥ 23/2019
በማዕከላዊ ሶማልያ መዱግ ክልል፣ ዱሳማረብ ከተማ እአአ ታኅሳሥ 23/2019

የሶማልያዋ ጋልሙዱግ ክልል ፕሬዚዳንት በመኪና ላይ ተጠምዶ ከነበረ ፈንጂ ጥቃት ያለምንም ጉዳት መትረፋቸውን ባለሥልጣናትና እማኞች ተናገሩ።

አል-ሻባብ ኃላፊነት የወሰደበት የአጥፍቶ ጠፊ አደጋ ዛሬ፤ ዓርብ የተጣለው በማዕከላዊ ሶማልያ መዱግ ክልል ውስጥ ላስ-ጋአሜይ በምትባል መንደር እንደነበረና በጥቃቱ ሁለት የሃገሪቱ እንደራሴዎች መቁሰላቸው መገለፁን የሶማልኛ አገልግሎት ባልደረባችን መሃመድ ኦላድ ዘግቧል።

ፍንዳታው የደረሰው እንደልማድ “ቆርቆር” በሚል ተቀጥያ ስም የሚታወቁት የጋልሙዱግ ክልል ፕሬዚዳንት አህመድ አብዲ ካሪዬ ካረፉበት ቦታ 300 ሜትር ርቀት ላይ እንደነበረ የአካባቢው ባለሥልጣናት አመልክተዋል።

እያካሄዱ ያሉት ዘመቻ የአልቃይዳ ጋር ግብርአበር የሆነውን “አልሸባብን በጥቂት ወራት ውስጥ ለማጥፋት የታለመ ነው” ሲሉ የሶማልያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ባለፈው ሳምንት ተናግረው ነበር።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG