በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻርለስ ሳተን የኢትዮጵያ ሙዚቃ አበርክቶ እና የተዘነጋው ውለታው


የቻርለስ ሳተን የኢትዮጵያ ሙዚቃ አበርክቶ እና የተዘነጋው ውለታው
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:35 0:00

አሜሪካዊው ቻርለስ ሳተን፣ በኢትዮጵያ ሙዚቃ እድገት ሒደት አሻራቸውን ካስቀመጡ ውለተኛ የውጭ ሀገር ዜጎች አንዱ እንደኾነ ይነገርለታል፡፡

በ1950ዎቹ መጨረሻ “የሰላም ጓድ” (Peace Corps) አባል ኾኖ ወደ ኢትዮጵያ ያቀናው ቻርለስ ሳተን በቆይታው፣ የባህል ሙዚቃ መሣርያ የኾነውን መሰንቆ ተምሮ፣ የዐማርኛ ዘፈኖችን ከኦርኬስትራ ኢትዮጵያ የባህል ቡድን ጋራ ተባብሮ በመድረክ እስከ ማቅረብ ደርሷል፡፡

አስማማው አየነው፣ በአሁኑ ወቅት የ81 ዓመት አዛውንት ከኾነው ቻርለስ ሳተን ጋራ በኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ ላይ ተጨዋውቷል፡፡ ኢትዮጵያውያን የሙዚቃ ባለሞያዎችንም አነጋግሮ፣ የ“ሰላም ጓዱ” ቻርለስ ሳተን፣ ለኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ እድገት ስላበረከተው አስተዋፅኦ የተሰናዳውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

XS
SM
MD
LG