በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ዐዲስ ዓመት ለኢኮኖሚዋ ከተስፋ ይልቅ ስጋት ያየለበት እንደኾነ ተጠቆመ


የኢትዮጵያ ዐዲስ ዓመት ለኢኮኖሚዋ ከተስፋ ይልቅ ስጋት ያየለበት እንደኾነ ተጠቆመ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:13 0:00

በዐማራ ክልል የተስፋፋው ጦርነት እና በኦሮሚያ ክልል የቀጠሉ አለመረጋጋቶች፣ ከኑሮ ውድነቱ ጋራ ተደማምሮ፣ ሀገራዊ ኢኮኖሚው በዐዲሱ ዓመትም በአስቸጋሪ ኹኔታ ውስጥ ሊያሳልፈው እንደሚችል፣ የፋይናንስ እና የምጣኔ ሀብት ምሁራን ስጋታቸውን ጠቆሙ፡፡

ባለፈው ዓመት በፕሪቶርያ የተፈረመው የሰላም ስምምነት፣ በጦርነት ለተዳከመው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ መነቃቃትንና ተስፋን የሰጠ እንደነበር ምሁራኑ አመልክተዋል፡፡

በአንጻሩም፣ በሸኘነው የ2015 ዓ.ም. ተስፋፍቶ የታየው የሰላም ዕጦት፣ በአጠቃላይ የምርት ሒደቱ ላይ ጫና እንደፈጠረና የዋጋ ንረትን ጨምሮ በርካታ ምጣኔ ሀብታዊ ችግሮችን እንዳስከተለ ምሁራኑ አውስተዋል፡፡ በዚኹ ሀገራዊ የሰላም ዕጦት አድማስ ሥር ዛሬ የባተው የኢትዮጵያ ዐዲስ ዓመትም፣ ለኢኮኖሚያዋ ከተስፋ ይልቅ ስጋትን አዝሎ የሚታይበት እንደኾነ፣ የፋይናንስ እና የምጣኔ ሀብት ምሁራኑ ጠቁመዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG