በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግጭት ከፈተና ያሰናከላቸው ከ15ሺሕ በላይ ተማሪዎች ከሳምንት በኋላ ይቀመጣሉ


ግጭት ከፈተና ያሰናከላቸው ከ15ሺሕ በላይ ተማሪዎች ከሳምንት በኋላ ይቀመጣሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:00 0:00

በኢትዮጵያ ባለፈው የ2015 ዓ.ም. ሐምሌ ወር የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና፣ በግጭት ምክንያት ያልወሰዱ ከ15ሺሕ በላይ ተማሪዎች፣ ከአንድ ሳምንት በኋላ ለፈተና እንደሚቀመጡ፣ የሀገሪቱ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ።

ተፈታኝ ተማሪዎቹ፣ በዐማራ ክልል በጎንደር ከተማ እና በጋምቤላ ክልል በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት፣ ፈተናውን ሙሉ በሙሉ እና በከፊል ያልወሰዱ መኾናቸውን ተቋሙ ጨምሮ ገልጿል።

ፈተናውን ከመጪው መስከረም 8 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ለመፈተን ዝግጅት እየተደረገ እንዳለ፣ የተቋሙ የሕዝብ ግንኙነት እና ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ሥራ አስፈጻሚ ማንጠግቦሽ አዳምጤ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG