በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በካርቱም በደረሰ የአየር ድብደባ ቢያንስ 40 ሰዎች ተገደሉ


ፎቶ ፋይል ኤፒ (ሰኔ 8፣ 2023)
ፎቶ ፋይል ኤፒ (ሰኔ 8፣ 2023)

በሱዳን መዲና ካርቱም ዛሬ እሁድ በደረሰ የአየር ድብደባ ቢያንስ 40 የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸውን እና በደርዘን የሚቆጠሩ ደግሞ መጎዳታቸውን በከተማዋ የሚገኙ ማኅበራዊ አንቂዎች ተናግረዋል።

የዛሬ ማለዳው ድብደባ ባለፈው ሚያዚያ ጦርነቱ ከጀመረ ወዲህ የተከሰተ አስከፊ እና ብዙ ሕይወት ከቀጠፉ ድብደባዎች አንዱ ነው ተብሏል።

የዲሞክራሲ አቀንቃኝ እና ጦርነቱ ከጀመረ ወዲህ ደግሞ ለተጎጂዎች ዕርዳታ በማድረግ ላይ ያለው ‘የአካባቢ ኮሚቴ’ እንዳለው፣ ዛሬ ጠዋት አንድ ሰዓት አካባቢ የደረሰው ድብደባ የተፈጸመው ‘ቆሮ’ በተባለ የገበያ ቦታ ነው። ተጎጂዎች ወደ ሆስፒታል በመምጣት ላይ በመሆናቸው የሟቾች ቁጥር ከተጠቀሰውም በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል ኮሚቴው ስጋቱን ገልጿል።

ግጭቱ ባለፈው ሚያዚያ ከጀመረ ወዲህ 7ሺሕ 500 የሚሆኑ ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ ዝቅተኛ ግምት አለ ሲል ‘የትጥቅ ግጭት ቦታዎች እና ክስተቶች ፕሮጀክት’ የተሰኘው ተቋም አስታውቋል።

የሱዳን ጦር ሰራዊት በሰማይ የበላይነቱን ሲያገኝ፣ ተፋላሚው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ደግሞ በካርቱም መንገዶችን በበላይነት እንደሚቆጣጠር የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

የሠራዊቱ መሪ አብደል ፋታህ አል ቡርሃን ከተቀናቃኛቸው አምዳን ዳግሎ ጋር የሚለዋወጡት ኃይለ ቃል እየቀጠለ ቢሆንም፣ በቅርቡ ወደ ግብጽ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኳታር ያደረጉት ጉዞ ወደ ዲፕሎማሲ ለመመለስ እንደሚሹ ፍንጭ ሰጥቷል ተብሏል።///

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG